በዲሲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (DCPS)፣ ለተማሪዎቻችን ሁሉ አዝናኝ እና ጠንካራ የትምህርት አስጣጥ ለማካሄድ በቁርጠኛነት ቆመ ናል። በየዕለቱ ከትምህርት ገበታ ላይ መገኘት እና ትምህርት መከታተል፣ ድጋፍ እና ፍቅርን ማግኘት፣ ተማሪዎች ወደ ስኬታማነት በሚ ያራምዳቸው ጥርጊያ ጎዳና ላይ ለማስቀመጥ እና ለማኖር ይረዳል።
ተማሪው በትምህርት ገበታ ላይ በማይገኝበት ሰዓት ማኅበረሰባችን ላይ ጫና ያሳድራል። የልጅዎ ከትምህርት ቤት መቅረት ምክንያት ያለው እና በይቅርታ የሚታለፍ ከሆነ፣ እባክዎን እንደ የሀኪም ወረቀት የመሰለ ድጋፍ ሰጪ ማስረጃ ለልጅዎ ትምህርት ቤት ያቅርቡ።
ልጅዎ ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄድ ወይንም ከትምህርት ገበታ ላይ በሰዓቱ እንዲገኝ የማድረግ ችግር ካለብዎት፣ የሚከተሉትን እንዲያደርጉ የመፍትሄ ሀሳብ እናቀርባለን፤
- ከትምህርት ቤትዎ አመራር ኃላፊ ጋር፣ ማኅበራዊ ጉዳይ ሠራተኛ፣ የሥነ ልቦና ባለሙያ፣ ወይንም መምህር ጋር መነጋገር፤
- ከትምህርት ቤቱ የጤና ሞግዚት ባለሙያዎች ጋር እና የሚቻልም ሆኖ ከተገኘ የግል የጤንነት እቅድ የአሞላል እርዳታ መጠየቅ፤
- የልጅዎን የአሁን ጊዜ ግላዊ የትምህርት እቅድ (Individual Education Plan (IEP))፣ ከትምህርት ቤት ኃላፊዎች ጋር አብሮ አንድ ላይ መመርመር እና/ወይም
- ሌሎች ድጋፍ ሰጪ አገልግሎቶች አካላትን ወይንም የሌሎች ባለሙያዎችን እርዳታ ለማግኝት ኣንዲቻል ለሌላ አካል ማስተላለፍ።
ለሁለተኛ ደረጃ እና ለመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ ከትምህርት ቤት ያለፈቃድ መቅረት፣ በአንድ የተወሰን የትም ህት ወቅት፣ የተማሪው ያለፈቅድ ለቀረበት ክፍልን ጨምሮ ለማንኛውም የትምህርት ዓመት አምስት ወይንም ከዚህ በላይ 10 ወይንም የበለጡ ቀሪዎች ካሉበት ከትምህርት ገበታ ላይ መቅረት በትምህርት ውጤት ነጥቦች ላይ ቀጥታ የሆነ ጫና ያሳድራል። ተማሪው በአ ንድ ሙሉ የትምህርት ዓመት ውስጥ 30 ወይንም ከዚህ በላይ ለሆኑ ለቀረባቸው ጊዜያት በዚያ ትምህርት እንደወደቀ ይቆጠራል።
ልጅዎ በየቀኑ ከትምህርት ቤት የሚገኙ መሆኑን ዕውን ለማድረግ ከእኛ ጋር በመጎዳኘትዎ እናመስግንዋታለን። ከላይ ተዘርዝረው ስለ ቀረቡት ድጋፎች ጥያቄዎች ካሉዎት፣ ወይንም ድጋፎቹን ለማግኘት ከፈልጉ እባክዎን ትምህርት ቤትዎን ያነጋግሩ።
ልጅዎን ከትምህርት ቤት ለማየት በጉጉት እንጠባበቃለን!