This page contains information about DCPS services for Amharic speakers.
DCPS፣ የእናንተን ቋንቋ ይናገራል!
እንኳን ወደ ኮሎምብያ ዲስትሪክት የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (DCPS) በሰላም መጣችሁ። ስልክ ስትደውሉ ወይም ለመነጋገር ስትመጡ፤ ካለምንም ክፍያ አስተርጓሚ በአካል እንዲቀርብላችሁ እና ከሠራተኛ አባሉ ጋር መነጋገር እንዲችሉ ወይም አስተርጓሚ በስልክ ቀርቦ በቋንቋችሁ እርዳታን እንድታገኙ በማድረግ ያገለግላችኋል።
የልጅዎን ትምህርት ቤት፣ ማነጋገር ካስፈለገዎት ወይም ማንኛውንም የDCPS ቢሮን በቋንቋዎ ለማነጋገር፣ እባክዎን ያሳውቁን። የልጅዎን አስተማሪ፣ የትምህርት ቤቱን ርዕሰ መምህር (Principal) ሊያሳውቁዋቸው የሚችሉ ሲሆን፤ ወይም ደግሞ የDCPS የቋንቋ ማግኛ ክፍልን በ(202) 868-6508 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።
“እናገራለሁ (I Speak)” የሚለውን ካርድ ጨምሮ፣ በቋንቋ እገዛ ማግኛ፣ የወላጅ መመሪያ (Parent’s Guide to Language Access) ፣ ዳውንሎድ (download) ማድረግና ማተም (print ማድረግ) ይችላሉ። ወደ ልጅዎ ትምህርት ቤት ሲመጡ ወይም የDCPS ቢሮን ለመጎብኘት ሲመጡ፣ በቋንቋዎ እርዳታን ለመጠየቅ ይዘውት ይምጡ። በቋንቋ ላይ ስለሚሰጡ አገልግሎቶች፣ ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት፤ እባካችሁን፣ ይህን ቪዲዮ ተመልከቱ።
በፍጥነት ሊያገኟቸው የሚችሏቸው ማገናኛዎች (Links)
- በቤት ውስጥ መማር ለልጅዎ ምን ሊመስል እንደሚችል፣ በቅርብ ጊዜ የወጣ መረጃዎች (The latest information on what learning at home will look like for your child)
- በDCPS ውስጥ ልጅዎን እንዴት ማስመዝገብ እንደሚችሉ፤ (How to enroll your child in DCPS)
- አድራሻዎ ላይ መሠረት ባደረገ ሁኔታ በክልል ወሰንዎ ውስጥ የሚገኘውን ትምህርት ቤት መፈለግ (Find your in-boundary school based on your address)
- እንግሊዘኛ ቋንቋን እንደ ሁለተኛ ቋንቋነት የሚማሩ ተማሪዎች (የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተማሪዎች)፤ (Students learning English as a second language (English Language Learners)
- የወላጆች የማወቅ መብት፣ መመሪያ (Parents’ Right to Know Guide)
- ሁለት ቋንቋ ፕሮግራሞች (Dual Language Programs)
- ከትምህርት በኋላ ፕሮግራሞች (Afterschool programs)
- በቋንቋ እገዛ ማግኛ፣ የወላጅ መመሪያ (Parent’s Guide to Language Access)
- “እናገራለሁ (I Speak)” ካርዶች (ከዲሲ የሰብ ዓዊ መብቶች ቢሮ የተሰጠ)